What the media says
የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን ዘግይተው ከተቀላቀሉት መካከል አንዱ የሆነው ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ ዓመታዊ ትርፉን ከሦስት እጥፍ በላይ ማሳደጉን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው የ2016 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሪፖርተር እንዳሳወቀው፣ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 181.3 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ ከታክስ በኋላ ያገኘው የትርፍ መጠን 151.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ከታክስ በፊትም ሆነ በኋላ ያገኘው ትርፍ […]