What the media says

 

የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን ዘግይተው ከተቀላቀሉት መካከል አንዱ የሆነው ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ ዓመታዊ ትርፉን ከሦስት እጥፍ በላይ ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የ2016 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሪፖርተር እንዳሳወቀው፣ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 181.3 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡

ከታክስ በኋላ ያገኘው የትርፍ መጠን 151.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ከታክስ በፊትም ሆነ በኋላ ያገኘው ትርፍ ኩባንያው ወደ ሥራ ከገባበት አራት ዓመት ወዲህ በከፍተኛነቱ የሚጠቀስ ነው፡፡ ዘመን ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት አግኝቶት የነበረው ትርፍ 45.9 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡

ኩባንያው በሒሳብ ዓመቱ የ545.3 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ ችሏል፡፡ ይህ የዓረቦን ዓረቦን ቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ67.5 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው፡፡ የዓረቦን ምጣኔውን በዚህ ደረጃ ማሳደግ መቻሉ፣ የዘመን ኢንሹራንስ ራሱን የገበያ ድርሻ ማሳደግ አስችሏል፡፡፡ ኩባንያው የቀደመው ዓመት ገበያ ድርሻው በ18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የነበረው ሲሆን፣ በተያዘው ሒሳብ ዓመት ግን ደረጃዎችን በማሻሻል ወደ 14ኛ  አሳድጓል፡፡

read the full story on this link.

https://www.capitalethiopia.com/2023/10/22/zemen-insurance-reports-seventeen-fold-increase-in-profits/