ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ.
Zemen Insurance S.C

የስብሰባ ጥሪ
ለዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የማህበሩ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ፡……. ብር 205,000,000
የምዝገባ ቁጥር…………………………የንግድ ምዝገባ ቁጥር MM/AA/3/005/867/2012
የኢንሹራንስ ሥራ ፈቃድ ቁጥር፡- 020/20 ዋና መሥሪያ ቤት፡ ክልል፡ አዲስ አበባ ክ/ከተማ፡ ቦሌ ወረዳ፡02 የቤት ቁጥር፡ 3140

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2012 አንቀጽ 366 (1)፣ 367(1)፣ 370 እና 393 እንዲሁም
በኩባንያው መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 10 መሰረት የዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ እና
3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 02፡00 ጀምሮ ቸርችል ጎዳና ወደ
ካቴድራል ት/ቤት መታጠፊያ ላይ በሚገኘው ግራንድ ኤልያና ሆቴል 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው መሰብሰቢያ
አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንዲገኙልን የኩባንያው
የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን እያሰተላለፈ በንግድ ህግ አንቀፅ 380 መሰረት የጉባኤው ድምጽ
ቆጣሪዎች ተሰይመው እና ምልዓተ ጉባኤው መሟላቱ ተረጋግጦ ጉባኤዎቹ የሚጀመሩ መሆኑን ይገልፃል፡፡

የ4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1. አጀንዳ ማፅደቅ፤
2. የኩባንያውን አክሲዮን ዝውውሮች እና አዳዲስ አክሲዮን የገዙ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
3. በማገልገል ላይ ያሉ ተተኪ የዳይሬክተሮች የቦርድ አባል ሹመት ማጽደቅ፤
4. እ.ኤ.አ የ2022/23 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ፣ መወያየትና በቀረበው ሪፖርት ላይ ውሳኔ ማሳለፍ፤
5. እ.ኤ.አ የ2022/23 የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥ፣ መወያየትና በቀረበው ሪፖርት ላይ ውሳኔማሳለፍ፤
6. እ.ኤ.አ ከ2023/24 የሒሳብ ዓመት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ አመታት የሚያገለግል የውጭ ኦዲተርመሾም፤
7. እ.ኤ.አ የ2023/24 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፤
8. እ.ኤ.አ የ2023/24 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ወርሃዊ አበልን መወሰን፤
9. እ.ኤ.አ የ2022/23 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዓመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን፤
10. እ.ኤ.አ የ2022/23 የሒሳብ ዓመት የትርፍ ድርሻ ክፍፍልን መወሰን፤
11. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፡፡

3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1. አጀንዳ ማፅደቅ፤
2. የተራፊ አክዮኖች ሽያጭን በሚመለከት የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
3. የኩባንያውን የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻል፤
4. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፡፡
ማሳሰቢያ፡-

ባለአክሲዮኖች ለስብሰባ በሚመጡበት ጊዜ ማንነትን የሚያረጋግጥ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይንም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጉባዔው ላይ በግንባር የማይገኙ ባለአክሲዮኖች፣ በንግድ ሕግ አንቀጽ 373 መሠረት፣ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ጉባኤው ከመካሄዱ ከሶስት ቀናት በፊት ቦሌ መንገድ ዓለም ሕንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት የማህበር ፀሃፊ ቢሮ ቀርበው ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ በያዘ ተወካይ አማካይነት በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤  በባለአክስዮኖች የተሰጠ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ የያዛችሁ ተወካዮች፡-

  • ማንነትን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት፣ ዋናውናቅጂውን፣
  • የወኪሉን የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይንም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ቅጂ፤ እንዲሁም
  • በጉባኤው ለመካፈልና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ዋናውን እና ቅጂውን ይዛችሁ በመቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት
    እናሳውቃለን፡፡

በባለአክስዮኖች የተሰጠ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ውክልና ያለው ተወካይ የራሱን/የራሷን ድምጽ መስጠት የሚያስችል አክሲዮኖችን ጨምሮ ከኩባያው የተፈረመ ካፒታል 10% በላይ ሊወክል/ልትወክል አይችልም/አትችልም፤
የተሻሻለውን የመመስረቻ ረቂቅ ሰነድ ከዋናው መሥሪያ ቤት የሕግ አገልግሎት ቢሮ ቀርባችሁ መውሰድ የምትችሉ ወይንም በኩባንያው ድረ ገፅ ላይ የተቀመጠ በመሆኑ ሰነዱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ቦሌ መንገድ ዓለም ሕንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያችን ዋና መሥሪያ ቤት
በአካል በመቅረብ፣ በስልክ ቁጥር 0115575850 በመደወል እና በኩባንያችን ድረገጽ-
www.zemeninsurance.com ማግኘት ይቻላል፡፡

የተሻሻለ የመመስረቻ ፅሑፍ

ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ