ለዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ. እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በሰኔ 18 ቀን 2019 ባወጣው መመሪያ ቁጥር 188/2020 መሠረት የዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክስዮኖች ባካሄዱት 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የቦርድ አባላት ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ መምረጡ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት ኮሚቴው መስፈርቱን የሚያሟሉ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማዎችን  ከሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ  ለመቀበል ዝግጅቱን ጨርሶ ባለአክሲዮኖችን ጥቆማ እንዲሰጡ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ለቦርድ አባልነት ምርጫ በዕጩነት የሚጠቆሙ ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

 1. ዕድሜው/ዋ 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነው/ናት እና በማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ/ና ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
 2. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ማህበሩ ከሚሰራቸው የንግድ ስራዎች እና ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ የጥቅም ግጭት በማይፈጥር ሥራ ላይ የተሰማራ/ች፤
 3. የትምህርት ደረጃ፡- ከጠቅላላ የቦርድ አባላት ቢያንስ 75% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና በተለይ የትምህርት ዝግጅቱ በኢንሹራንስ ሥራ፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በኦዲት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት የሆነ እና ቀሪው 25% ደግሞ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ/ች መሆን ይኖርባቸዋል፤
 4. የሥራ ልምድ- በንግድ ሥራ አመራር ወይም በኢንሹራንስ ሥራ በቂ ልምድ ያለው/ያላት ቢሆን ተመራጭ ሆኖ በኢንሹራንስ ሥራ፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በኦዲት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት ልምድ ያለው/ያላት ወይም ከተመረጠ/ች በኋላ ስለኢንሹራንስ ሥራ ማኔጅመንት ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
 5. በሌላ ተወዳዳሪ ፋይናንስ ተቋም የቦርድ አባል ያልሆነ/ች፤
 6. የዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሜቴ አባል ያልሆነ/ች፤
 7. የሕግ ሰውነት ያለው ድርጀት በእጩነት የሚጠቆም ከሆነ ድርጅቱን በዳይሬክተሮች ቦርድ የሚወክለው ግለሰብ (የተፈጥሮ ሰው) አብሮ ሊጠቆም ይገባል፡፡ ግለሰቡም የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ እና በተጠቋሚው ድርጅት ውስጥ 10% እና ከዚያ በላይ የአክስዮን ድርሻ የሌለው ሊሆን ይገባል፤
 8. በኢትዮጵያና ከኢትዮጲያ ውጭ የእምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ/ችና በፍ/ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት/ባት፤ በኢትዮጵያ ወይም ከኢትዮጵያ ውጪ ባለ በፈረሰ ተቋም ዳይሬክተር ያልነበረ/ች ወይም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቅድሚያ ፈቃድ ሊያቀርብ የሚችል/የምትችል፤ ከመምረጥና መመረጥ መብት ያልተገደበ/ች፤
 9. በተ.ቁ 8 ከተጠቀሰው በተጨማሪ መልካም ሥነ-ምግባርና ማኅበራዊ ተቀባይነት ያለው ሆኖ/ና በንግድ ማኅበር አደራጅነት፣ ዳይሬክተርነት፣ ስራ አስኪያጅነት፣ ተቆጣጣሪነት፣ ኦዲተርነት ወይም በሌሎች የአመራር ኃለፊነቶች ላይ ተመድቦ ሲሰራ/ስትሰራ ከሃላፊነቱ/ቷ ጋር በተያያዘ ወይም በማንኛውም ሁኔታ በእምነት ማጉደል በስረቆት ወይም በውንብድና ወይም ለቦርድ አባላነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ ወንጀል ጥፋተኛነቱ/ቷ ያልተረጋጋጠ፣
 10. የፋይናንሽያል ጤናማነትን መስፈርት የሚያሟላ ማለትም በኪሳራ ላይ ያልሆነ/ች የታክስና የባንክ ግዴታዎቹን የተወጣ/ች፤
 11. የጾታ ተዋጽኦን ያማከለ፤
 12. ሌሎች በብሔራዊ ባንክ የተጠቀሱ መመዘኛዎችን/መሥፈርቶችን የሚያሟላ/የምታሟላ፡፡

ማሳሰቢያ

 1. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዘጠኝ አባላት የሚኖሩት ሲሆን ለምርጫ የሚቀርቡ አጠቃላይ እጩዎች ብዛት 18 ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1/3 ኛው (6ቱ) እጩዎች የሚጠቆሙት ከማኅበሩ ጠቅላላ አክሲዮን 2% በታች በያዙ ባለአክሲዮኖች ሲሆን ቀሪው 2/3ኛዉ (12ቱ) እጩዎች ደግሞ በሁሉም ባለአክሲዮኖች በጋራ የሚጠቆሙ ይሆናሉ፤
 2. ነባር የቦርድ አባላት በእጩነት ሊቀርቡ ይችላሉ፤
 3. የጥቆማ መስጫ ቅጹን፣ የተጠቋሚዎችን መሥፈርት እና የጥቆማ መመዘኛ የያዙትን አግባብነት ያላቸው የብሔራዊ ባንክ መመሪያዎቹን ከማህበሩ ድረ-ገጽ zemeninsurance.com ማውረድ እና መመልከት ይቻላል፤
 4. የጥቆማ መስጫ ቅጾችን ከማኅበሩ ዋና መ/ቤት እና ከሁሉም የማኅበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማግኘት ይቻላል፤
 5. ጠቋሚዎች ራሳቸውን ተጠቋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባል አድርገው ማቅረብ ይችላሉ፤
 6. ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፤
 7. በአካል ጥቆማ ለምታደርጉ “ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት እጩ ጥቆማ ማቅረቢያ ቅጽ” በሚል የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በማኅበሩ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ቦሌ መንገድ፣ ዓለም ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ እንዲሁም በማኅበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመገኘት በአካል ቀርቦ በማስመዝገብ መጠቆም ይቻላል፤
 8. ተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ፡- ከኩባንያው ድረ-ገጽ zemeninsurance.com እንዲሁም በስልክ ቁጥር 0911-814303 እና 0911-148193 በመደወል ማግኘት ይቻላል፤
 9. በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መስፈርቱን የሚያሟሉ እጩዎች ለአስመራጭ ኮሜቴ በአማራጭነት በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ፡፡
 • በፋክስ ቁጥር፡- +251 116 150 001
 • በኢሜይል አድራሻ፡-nomele2022@zemeninsurance.com

የዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ